በችግር ቀን እግዚአብሔር ጸሎትህን ይስማ! የያዕቆብ አምላክም ስም ይጠብቅህ! ከመቅደሱ ርዳታውን ይላክልህ፤ ከጽዮን ተራራም ይደግፍህ። መባህን ሁሉ ይቀበልልህ፤ በመሥዋዕትህም ደስ ይበለው። የልብህን ምኞት ይስጥህ፤ ሐሳብህን ሁሉ ይፈጽምልህ፤ ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤ በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ። እግዚአብሔር ቀብቶ ያነገሠውን እንደሚረዳ አሁን ዐውቃለሁ፤ በቀኝ እጁ ታላቅ ድልን በማቀዳጀት ከተቀደሰው ቦታ ከሰማይ ለጸሎቱ መልስ ይሰጠዋል። አንዳንዶች በጦር ሠረገሎቻቸው፥ ሌሎችም በፈረሶቻቸው ይመካሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ኀይል እንታመናለን።
መጽሐፈ መዝሙር 20 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 20:1-7
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች