መጽሐፈ መዝሙር 18:46-50

መጽሐፈ መዝሙር 18:46-50 አማ05

እግዚአብሔር ሕያው ነው! አምላኬ መጠጊያዬ ይመስገን! ያዳነኝም ኀያል አምላክ ከፍ ከፍ ይበል። እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል። ከጠላቶቼም ታድነኛለህ። ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፤ ከግፈኞችም ታድነኛለህ። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህ በሕዝቦች መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ለስምህም እዘምራለሁ። እርሱ ላነገሠው ንጉሥ ታላቅ ድልን ያጐናጽፈዋል፤ ራሱ ለቀባው ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳየዋል፤ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘለዓለም ይህን ያደርጋል።