መዝሙር 18:46-50

መዝሙር 18:46-50 NASV

እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተባረከ ይሁን! የድነቴ አምላክ ከፍ ከፍ ይበል። እርሱ በቀሌን የሚመልስልኝ፣ አሕዛብንም የሚያስገዛልኝ አምላክ ነው፤ ከጠላቶቼም የሚታደገኝ እርሱ ነው። አንተ ከባላንጦቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኞች አዳንኸኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፤ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ ስምህንም በመዝሙር እወድሳለሁ። እርሱ ላነገሠው ታላላቅ ድሎችን ይሰጣል፤ ጽኑ ፍቅሩንም ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይገልጣል።