መጽሐፈ መዝሙር 149:6-9

መጽሐፈ መዝሙር 149:6-9 አማ05

ስለ ታም ሰይፍ በእጆቻቸው ይዘው እልል እያሉ እግዚአብሔርን በከፍተኛ ድምፅ ያመስግኑት። እንደዚህ ቢያደርጉ መንግሥታትን ለማሸነፍ፥ አሕዛብንም ለመቅጣት፥ ንጉሦቻቸውን በሰንሰለት ለመያዝ፥ መኳንንቶቻቸውን በእግር ብረት ለማሰር፥ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የደነገገውን በመፈጸም የእግዚአብሔር ሕዝቦች ድልን ይጐናጸፋሉ።