መዝሙር 149:6-9
መዝሙር 149:6-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርን በጕሮሮአቸው ያመሰግኑታል፤ ሁለት አፍ ያለውም ሰይፍ በእጁ ነው፥ በአሕዛብ ላይ በቀልን ያደርግ ዘንድ፥ ሕዝቡንም ይዘልፋቸው ዘንድ፤ ንጉሦቻቸውንም በእግር ብረት፥ አለቆቻቸውንም በሰንሰለት ያስራቸው ዘንድ፤ የተጻፈውን ፍርድ በእነርሱ ላይ ያደርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻድቃኑ ሁሉ ናት።
መዝሙር 149:6-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የአምላክ ውዳሴ በአንደበታቸው፣ ባለሁለት ልሳን ሰይፍም በእጃቸው ይሁን፤ በዚህ ሕዝቦችን ይበቀላሉ፤ ሰዎችንም ይቀጣሉ፤ ነገሥታታቸውን በሰንሰለት፣ መኳንንታቸውንም በእግር ብረት ያስራሉ፤ ይህም በእነርሱ ላይ የተጻፈውን ፍርድ ለመፈጸም ነው። ለቅዱሳኑም ሁሉ ይህች ክብር ናት።