የባሕር አራዊትና የውቅያኖስ ጥልቀቶች እግዚአብሔርን ከምድር አመስግኑ። እሳትና በረዶ፥ ዐመዳይና ደመና፥ ትእዛዙን የምትፈጽሙም ብርቱዎች ነፋሳት እግዚአብሔርን አመስግኑ። ኰረብቶችና ተራራዎች፥ የፍሬ ተክሎችና የደን ዛፎች ሁሉ አመስግኑት። አራዊትና ለማዳ እንስሶች፥ በምድር የምትሳቡና በክንፍ የምትበርሩ ፍጥረቶች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት። ነገሥታትና የምድር ሕዝቦች፥ መሳፍንትና ፈራጆች ሁሉ አመስግኑት። ጐልማሶችና ልጃገረዶች፥ ሽማግሌዎችና ልጆች ሁሉ አመስግኑት። የእርሱ ስም ከሌሎች ስሞች ስለሚበልጥና ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ስለ ሆነ ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! ለእርሱ ቅርብ የሆኑትን ታማኝ አገልጋዮቹን እስራኤልን ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ምስጋናንም አቀዳጃቸው። እግዚአብሔርን አመስግኑ!
መጽሐፈ መዝሙር 148 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መዝሙር 148:7-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች