መጽሐፈ መዝሙር 141
141
የማታ ጸሎት
1እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ እጣራለሁ፤
በፍጥነትም እርዳኝ!
ወደ አንተም ስጮኽ ስማኝ!
2ጸሎቴን እንደ ዕጣን፥
የተዘረጉትን እጆቼን እንደ ማታ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበል። #ራዕ. 5፥8።
3እግዚአብሔር ሆይ! ለአፌ ጠባቂ አኑር፤
በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።
4ስሕተት ለማድረግ ከመመኘትና
ከክፉ አድራጊዎች ጋር በክፉ ሥራ ከመተባበር ጠብቀኝ፤
የበዓላቸው ግብዣ ተካፋይ ከመሆን ጠብቀኝ።
5ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤
ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤
ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
6ዳኞቻቸው በገደል አለት ላይ በተጣሉ ጊዜ
ሕዝቦቻቸው የእኔ ቃል እውነት መሆኑን ያረጋግጣሉ።
7መሬት እንደሚታረስና ጓሉ እንደሚፈራርስ
የእነርሱም አጥንቶች በመቃብር አፍ ላይ ይበታተናሉ።
8እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ!
እኔ ግን በአንተ መተማመኔን አልተውም፤
የአንተንም ጥበቃ ስለምፈልግ እንድሞት አታድርገኝ!
9ከዘረጉብኝ ወጥመድ ጠብቀኝ፤
ከክፉ አድራጊዎችም መሰናክል አድነኝ።
10እኔ ያለ ጒዳት ሳልፍ
ክፉዎች ባጠመዱት ወጥመድ ይያዙ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 141: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997