መጽሐፈ መዝሙር 136
136
የምስጋና መዝሙር
1ቸር ስለ ሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርቡ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #1ዜ.መ. 16፥34፤ 2ዜ.መ. 5፥13፤ 7፥3፤ ዕዝ. 3፥11፤ መዝ. 100፥5፤ 106፥1፤ 107፥1፤ 118፥1፤ ኤር. 33፥11።
2ከአማልክት ሁሉ ለሚበልጠው አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
3የጌቶች ጌታ ለሆነው አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
4እርሱ ብቻ ታላላቅ ተአምራትን ያደርጋል፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
5በጥበቡ ሰማያትን ፈጠረ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፍ. 1፥1።
6ምድርን በጥልቅ ውሃዎች ላይ መሠረተ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፍ. 1፥2።
7ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
8ፀሐይ በቀን እንዲያበራ አደረገ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
9ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያበሩ አደረገ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፍ. 1፥16።
10የግብጻውያንን የበኲር ወንዶች ልጆች ገደለ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፀ. 12፥29።
11የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ አገር መርቶ አወጣ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፀ. 12፥51።
12በኀያልነቱና በሥልጣኑ ይህን አደረገ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
13ቀይ ባሕርን ከፈለ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
14እስራኤልንም በመካከሉ አሳለፈ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
15የግብጽን ንጉሥና ሠራዊቱን
በቀይ ባሕር አሰጠመ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘፀ. 14፥21-29።
16ሕዝቡን በበረሓ መራ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
17ታላላቅ ነገሥታትን ገደለ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
18ኀያላን ነገሥታትንም ደመሰሰ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
19የአሞራውያንን ንጉሥ ሲሖንን ገደለ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘኍ. 21፥21-30።
20የባሳንንም ንጉሥ ዖግን ገደለ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። #ዘኍ. 21፥31-35።
21ምድራቸውን ሁሉ ለሕዝቡ ርስት አድርጎ ሰጠ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
22ለአገልጋዩ ለእስራኤል አወረሰ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
23በተሸነፍን ጊዜ አልረሳንም፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
24ከጠላቶቻችን እጅ ነጻ አወጣን፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
25ለሥጋ ለባሽ ፍጥረት ሁሉ ምግብን ይሰጣል፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
26ይህን ሁሉ ስላደረገ ለሰማይ አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤
ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 136: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997