መጽሐፈ መዝሙር 137
137
በምርኮ የነበሩ እስራኤላውያን ለቅሶ
1በባቢሎን ወንዞች አጠገብ ተቀምጠን፥
ጽዮንን ባስታወስናት ጊዜ አለቀስን።
2እዚያ በገናዎቻችንን በአኻያ ዛፎች ላይ ሰቀልን።
3የማረኩንና ሥቃይ የሚያሳዩን ሰዎች
በመዘመር እንድናስደስታቸው
“ከጽዮን መዝሙሮች አንዱን ለእኛ ዘምሩልን” አሉን።
4ለእግዚአብሔር መቅረብ የሚገባውን መዝሙር
በባዕድ አገር እንዴት እንዘምራለን?
5ኢየሩሳሌም ሆይ! አንቺን ብረሳሽ
በገና የምጫወትበት ቀኝ እጄ ይክዳኝ፤
6አንቺን ባላስታውስሽና ታላቅ ደስታዬ አድርጌ ባልቈጥርሽ
ምላሴ ከትናጋዬ ይጣበቅ።
7እግዚአብሔር ሆይ! ኢየሩሳሌም በተያዘችበት ቀን
ኤዶማውያን ያደረጉትን አስብ፤
“እስከ መሠረትዋ አፈራርሳችሁ ጣሉአት!” እያሉ
መጮኻቸውንም አስታውስ።
8ባቢሎን ሆይ! አፍራሽዋ ባቢሎን!
በእኛ ላይ ያደረግሽብንን የክፋት ብድራት ሁሉ
በአንቺ ላይ የሚመልስብሽ የተባረከ ነው።
9ሕፃናት ልጆችሽን እያነሣ በአለት ላይ
የሚፈጠፍጣቸው የተባረከ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ መዝሙር 137: አማ05
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
© The Bible Society of Ethiopia, 2005
© የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር፥ 1997