የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 119:105-112

መጽሐፈ መዝሙር 119:105-112 አማ05

ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው። እውነተኛ ትእዛዞችህን ለመጠበቅ በመሐላ የገባሁትን ቃል አጸናለሁ። እግዚአብሔር ሆይ! ሥቃዬ እጅግ ከባድ ስለ ሆነ በተስፋ ቃልህ መሠረት በሕይወት አኑረኝ። እግዚአብሔር ሆይ! የምስጋና ጸሎቴን ተቀበል፤ ትእዛዞችህንም አስተምረኝ። ሕይወቴ በአደጋ ላይ ቢሆንም እንኳ ሕግህን አልረሳም ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ እኔ ግን ከትእዛዞችህ ፈቀቅ አላልኩም። ሕግህ ዘለዓለማዊ ሀብቴ ነው፤ የልቤም ደስታ እርሱ ነው። እስከምሞትበት ቀን ድረስ ሕጎችህን ለመፈጸም ወስኜአለሁ፤