የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ መዝሙር 100

100
የምስጋና መዝሙር
1በምድር ላይ የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ
ለእግዚአብሔር “እልል!” በሉ!
2እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት!
የደስታ መዝሙር እየዘመራችሁ ወደ እርሱ ፊት ቅረቡ!
3እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤
የፈጠረን እርሱ ነው፤ እኛ የእርሱ ነን፤
ስለዚህ እኛ እንደ በጎች መንጋ የሚያሰማራን ሕዝቦቹ ነን።
4እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤
ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤
አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ።
5እግዚአብሔር ቸር ነው፤
ፍቅሩና ታማኝነቱ ዘለዓለማዊ ነው። #1ዜ.መ. 16፥34፤ 2ዜ.መ. 5፥13፤ 7፥3፤ ዕዝ. 3፥11፤ መዝ. 106፥1፤ 107፥1፤ 118፥1፤ 136፥1፤ ኤር. 33፥11።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ