ቤተሰብዋ በሙሉ ሞቃት ልብስ ስላለው በረዶ እንኳ ቢዘንብ አትሠጋም። የአልጋ ልብስ ትሠራለች፤ ከቀይ ሐር የተሠራ ምርጥ ልብስም ትለብሳለች። ባልዋ የአገር ሽማግሌዎች በሚሰበሰቡበት ሸንጎ የተከበረ ነው። የበፍታ ልብስ እየሠራች ትሸጣለች፤ ለነጋዴዎችም ድግ ታስረክባለች። እርስዋ ብርቱና የተከበረች ናት፤ በመጪው ጊዜ ሁሉ ደስ ብሎአት ትኖራለች። በጥበብ ትናገራለች፤ በቅን መንፈስ ትመክራለች። ዘወትር በሥራ ተጠምዳ ቤተሰብዋን ስለምትንከባከብ ስንፍና አይገኝባትም። ልጆችዋ አድናቆታቸውን ይገልጡላታል፤ ባልዋም ያመሰግናታል፤ “ጥሩ ሚስቶች የሆኑ ብዙ ሴቶች አሉ፤ አንቺ ግን ከሁሉም ትበልጫለሽ” ይላታል። ቊንጅና ከንቱ ነው፤ ውበትም ይጠፋል፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን ልትመሰገን ይገባታል። እርስዋ ለምታደርገው ነገር ሁሉ አመስግኑአት፤ ስለ መልካም ሥራዋ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ልትከበር ይገባታል።
መጽሐፈ ምሳሌ 31 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 31:21-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች