መጽሐፈ ምሳሌ 16:20-22

መጽሐፈ ምሳሌ 16:20-22 አማ05

ለሚሰጠው ምክር ትኲረትን የሚሰጥ ይበለጽጋል፤ በእግዚአብሔርም የሚተማመን የተባረከ ነው። በአስተሳሰብ መብሰል ጥበበኛነትን ያመለክታል፤ ጣዕም ባለው አነጋገር መናገር ሌሎችን ያስተምራል። ጥበብን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሞኞች ግን በሞኝነታቸው ይቀጣሉ።