ምሳሌ 16:20-22

ምሳሌ 16:20-22 NASV

ምክርን የሚሰማ ይለመልማል፤ በእግዚአብሔርም የሚታመን ብፁዕ ነው። ልባቸው ጠቢብ የሆነ አስተዋዮች ይባላሉ፤ ደስ የሚያሰኙ ቃላትም ዕውቀትን ያዳብራሉ። ማስተዋልን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ቂልነት ግን በቂሎች ላይ ቅጣት ታመጣባቸዋለች።