እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ እስራኤላውያን በየተመደቡበት ቡድን ሰንደቅ ዓላማና በየነገዳቸው ዐርማ ሥር ይሰፍራሉ፤ አሰፋፈራቸውም የመገናኛው ድንኳን በዙሪያው ሆኖ ፊታቸው ከድንኳኑ ትይዩ ይሆናል። ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው። የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር። በእርሱም አጠገብ የሚሰፍሩት የይሳኮር ነገድ ይሆናሉ፤ የይሳኮር መሪም የጾዓር ልጅ ናትናኤል ነበር፤ የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ኀምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበር። ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎንም ልጆች መሪ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር። የእርሱም ክፍል ሰው ብዛት ኀምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበር። እንደየክፍላቸው በይሁዳ ሰፈር እንዲሰፍሩ የተደረጉት ሰዎች ብዛት መቶ ሰማኒያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ነበር። በመጀመሪያ የሚጓዘው ይህ ቡድን ነበር።
ኦሪት ዘኊልቊ 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘኊልቊ 2:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች