እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።” በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ፤ የይሁዳ ምድብ፤ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤ የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺሕ ስድስት መቶ ነው። ከእነዚህ ቀጥሎ የይሳኮር ነገድ ይሰፍራል፤ የይሳኮር ሕዝብ አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ አራት ሺሕ አራት መቶ ነው። ከዚያም የዛብሎን ነገድ ይቀጥላል፤ የዛብሎን ሕዝብ አለቃ የኬሎን ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣ የሰራዊቱም ብዛት ዐምሳ ሰባት ሺሕ አራት መቶ ነው። በየሰራዊታቸው ሆነው ከአይሁድ ምድብ የተመዘገቡ አንድ መቶ ሰማንያ ስድስት ሺሕ አራት መቶ ናቸው፤ እነዚህ አስቀድመው ይወጣሉ።
ዘኍልቍ 2 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘኍልቍ 2
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘኍልቍ 2:1-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos