የማርቆስ ወንጌል 3:1-6

የማርቆስ ወንጌል 3:1-6 አማ05

ኢየሱስ እንደገና ወደ ምኲራብ ገባ፤ እዚያም አንድ እጀ ሽባ ሰው ነበር። ኢየሱስን ሊከሱት የፈለጉ ሰዎች፥ “እስቲ በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ እንይ!” ብለው ይጠባበቁት ነበር። ኢየሱስም እጀ ሽባውን ሰው፦ “ና በመካከል ቁም” አለው። ከዚያም በኋላ “ለመሆኑ በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ። ኢየሱስም ስለ ልባቸው ድንዛዜ አዝኖ በዙሪያው ያሉትን በቊጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ” አለው። እርሱም በዘረጋ ጊዜ እጁ ዳነለት። ወዲያውኑ ፈሪሳውያን ወጥተው እንዴት አድርገው ኢየሱስን እንደሚያጠፉት ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ተማከሩ።

ተዛማጅ ቪዲዮዎች