በሌላ ጊዜ ወደ ምኵራብ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለች ሰው ነበር። በምክንያት ሊከስሱት የሚፈልጉ ሰዎችም በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደ ሆነ ለማየት ይጠባበቁ ነበር። እርሱም እጁ የሰለለችበትን ሰው፣ “ተነሥተህ መካከል ላይ ቁም” አለው። ኢየሱስም፣ “በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ? ሕይወት ማዳን ነው ወይስ ማጥፋት?” አላቸው። እነርሱ ግን ዝም አሉ። በልባቸው ደንዳናነት ዐዝኖ በዙሪያው የቆሙትን በቍጣ ተመለከታቸውና ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ!” አለው፤ ሰውየውም እጁን ዘረጋ፤ እጁም ፍጹም ደኅና ሆነችለት። ፈሪሳውያንም እንዴት እንደሚገድሉት ከሄሮድስ ወገን ከሆኑት ጋራ መመካከር ጀመሩ።
ማርቆስ 3 ያንብቡ
ያዳምጡ ማርቆስ 3
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ማርቆስ 3:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች