ኢየሱስ፥ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ። ከዚህ በኋላ አንድ የሕግ መምህር፥ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ “መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ ልከተልህ” አለው። ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ “ጌታ ሆይ መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው። ኢየሱስም “አንተ እኔን ተከተለኝ፤ ሙታንን ግን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው” አለው። ኢየሱስም ወደ ጀልባ ሲገባ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። ታላቅ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ስለ ተነሣ ማዕበሉ ጀልባይቱን ሊያሰጥማት ደረሰ፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፤ አድነን!” ብለው ቀሰቀሱት። እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም ተደንቀው፥ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” አሉ።
የማቴዎስ ወንጌል 8 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የማቴዎስ ወንጌል 8:18-27
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos