ማቴዎስ 8:18-27
ማቴዎስ 8:18-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ፣ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዛቸው። በዚህ ጊዜ አንድ የአይሁድ ሃይማኖት መምህር ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፤ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት ቦታ የለውም” ሲል መለሰለት። ደቀ መዝሙር የሆነ አንድ ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፤ መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው። ኢየሱስ ግን፣ “ሙታን ሙታናቸውን ይቅበሩ፤ አንተ ተከተለኝ” አለው። ከዚያም ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገብተው ሄዱ። ድንገት ኀይለኛ ማዕበል በባሕሩ ላይ ተነሥቶ ጀልባዪቱን እስኪሸፍን ድረስ አወካቸው፤ በዚህ ጊዜ ግን ኢየሱስ ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው ቀሰቀሱትና፣ “ጌታ ሆይ! ጠፋን፤ አድነን” አሉት። ኢየሱስም፣ “እናንተ እምነት የጐደላችሁ፤ ለምን ይህን ያህል ፈራችሁ?” አላቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ማዕበሉን ገሠጸ፤ ወዲያውም ጸጥታ ሰፈነ። ሰዎቹም፣ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት፣ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” እያሉ ተደነቁ።
ማቴዎስ 8:18-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ፥ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ። ከዚህ በኋላ አንድ የሕግ መምህር፥ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፥ “መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ ልከተልህ” አለው። ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ “ጌታ ሆይ መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው። ኢየሱስም “አንተ እኔን ተከተለኝ፤ ሙታንን ግን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው” አለው። ኢየሱስም ወደ ጀልባ ሲገባ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። ታላቅ ዐውሎ ነፋስ በባሕሩ ላይ ስለ ተነሣ ማዕበሉ ጀልባይቱን ሊያሰጥማት ደረሰ፤ ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፤ አድነን!” ብለው ቀሰቀሱት። እርሱም “እናንተ እምነት የጐደላችሁ! ስለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው። ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም ተደንቀው፥ “ነፋስና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” አሉ።
ማቴዎስ 8:18-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። አንድ ጸሐፊም ቀርቦ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። ኢየሱስም “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም፤” አለው። ከደቀ መዛሙርቱም ሌላው “ጌታ ሆይ! አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው። ኢየሱስ “ተከተለኝ፤ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤” አለው። ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! አድነን፤ ጠፋን፤” እያሉ አስነሡት። እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም “ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው?” እያሉ ተደነቁ።
ማቴዎስ 8:18-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። አንድ ጻፊም ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው። ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው። ከደቀ መዛሙርቱም ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ እንድሄድ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው። ኢየሱስም፦ ተከተለኝ፥ ሙታናቸውንም እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው አለው። ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆም ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ በባሕር ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው፦ ጌታ ሆይ፥ አድነን፥ ጠፋን እያሉ አስነሡት። እርሱም፦ እናንተ እምነት የጎደላችሁ፥ ስለ ምን ትፈራላችሁ? አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፥ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም፦ ነፋሳትና ባሕርስ ስንኳ የሚታዘዙለት፥ ይህ እንዴት ያለ ሰው ነው? እያሉ ተደነቁ።
ማቴዎስ 8:18-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በአጠገቡ ሲሰበሰቡ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። አንድ ጸሐፊ መጥቶ “መምህር ሆይ! ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጉድጓድ፥ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት የለውም፤” አለው። ከደቀ መዛሙርቱም አንዱ “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው። ኢየሱስም “ተከተለኝ፤ ሙታንን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤” አለው። ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ተከተሉት። እነሆ ማዕበሉ ጀልባይቱን እስኪሸፍናት ድረስ በባሕሩ ላይ ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ እርሱ ግን ተኝቶ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ጌታ ሆይ! ልንጠፋ ነው፥ አድነን፤” እያሉ ቀሰቀሱት። እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ። ሰዎቹም “ነፋሳትና ባሕር እንኳ የሚታዘዙለት፥ ይሄ ማነው?” እያሉ ተደነቁ።