የማቴዎስ ወንጌል 19:1-6

የማቴዎስ ወንጌል 19:1-6 አማ05

ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ካበቃ በኋላ ከገሊላ ተነሥቶ፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደምትገኝ ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ ከእነርሱም የታመሙትን እዚያ ፈወሳቸው። በዚያን ጊዜ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀረቡና ሊፈትኑት ፈልገው፥ “ሰው ሚስቱን በማንኛውም ምክንያት እንዲፈታ ይፈቀድለታልን?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? ደግሞም ‘በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይዋሓዳል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ’ ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አንድ አካል ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። እንግዲህ እግዚአብሔር አጣምሮ አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው።”

ተዛማጅ ቪዲዮዎች