ማቴዎስ 19:1-6
ማቴዎስ 19:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ በዚያም ፈወሳቸው። ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት “ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” አሉት። እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፤ አለም ‘ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤’ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።”
ማቴዎስ 19:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፣ ገሊላን ትቶ ከዮርዳኖስ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተለው፤ በዚያም ፈወሳቸው። ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት ቀርበው፣ “አንድ ሰው በማንኛውም ምክንያት ሚስቱን እንዲፈታ ተፈቅዷልን?” ሲሉ ጠየቁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? እንዲህም አለ፤ ‘ስለዚህ፣ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋራ ይጣመራል፣ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ’ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”
ማቴዎስ 19:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢየሱስም ይህን ነገር ከፈጸመ በኋላ፥ ከገሊላ ሄዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ መጣ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፥ በዚያም ፈወሳቸው። ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሲፈትኑት፦ ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን? አሉት። እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ አለም፦ ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል፥ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ የሚለውን ቃል አላነበባችሁምን? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደ ፊት ሁለት አይደሉም። እግዚአብሔር ያጣመረውን እንግዲህ ሰው አይለየው።
ማቴዎስ 19:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢየሱስ ይህን ተናግሮ ካበቃ በኋላ ከገሊላ ተነሥቶ፥ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደምትገኝ ወደ ይሁዳ ምድር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ ከእነርሱም የታመሙትን እዚያ ፈወሳቸው። በዚያን ጊዜ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀረቡና ሊፈትኑት ፈልገው፥ “ሰው ሚስቱን በማንኛውም ምክንያት እንዲፈታ ይፈቀድለታልን?” ሲሉ ጠየቁት። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸው አላነበባችሁምን? ደግሞም ‘በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይዋሓዳል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ’ ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አንድ አካል ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። እንግዲህ እግዚአብሔር አጣምሮ አንድ ያደረገውን ሰው አይለየው።”
ማቴዎስ 19:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ፥ ከገሊላ ወጥቶ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃ መጣ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት፤ እርሱም እዚያ ፈወሳቸው። ፈሪሳውያንም ወደ እርሱ ቀረቡና ሊፈትኑት ፈልገው “ሰው በማንኛውም ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን?” አሉት። እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ “ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት እንዳደረጋቸው አላነበባችሁምን? ዓለም ‘በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።’ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ሁለት አይደሉም። ስለዚህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው።”