የሉቃስ ወንጌል 7:44-46

የሉቃስ ወንጌል 7:44-46 አማ05

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ሴትዮዋ መለስ ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ “ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ስገባ አንተ ውሃ እንኳ ለእግሬ አላቀረብክልኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን በእንባዋ አጥባ በጠጒርዋ አበሰችው። አንተ ስትቀበለኝ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን እኔ ወደ ቤትህ ከገባሁ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም፤ አንተ ራሴን ዘይት እንኳ አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሮቼን ሽቶ ቀባች፤