ሉቃስ 7:44-46
ሉቃስ 7:44-46 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፥ “ይህቺን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ ለእግሮች ውኃ ስንኳ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን አልቅሳ በእንባዋ እግሬን አራሰች፤ በጠጕርዋም አበሰች። አንተስ ሰላምታ አልሰጠኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባችኝ።
ያጋሩ
ሉቃስ 7 ያንብቡሉቃስ 7:44-46 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፤ “ይህችን ሴት ታያታለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፤ አንተ ለእግሮቼ ውሃ እንኳ አላቀረብህልኝም፤ እርሷ ግን እግሮቼን በእንባዋ እያራሰች በጠጕሯ አበሰች። አንተ ከቶ አልሳምኸኝም፤ እርሷ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሮቼን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ እርሷ ግን እግሮቼን ሽቱ ቀባች።
ያጋሩ
ሉቃስ 7 ያንብቡሉቃስ 7:44-46 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ ሴቲቱም ዘወር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፦ ይህችን ሴት ታያለህን? እኔ ወደ ቤትህ ገባሁ፥ ውኃ ስንኳ ለእግሬ አላቀረብህልኝም፤ እርስዋ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች በጠጕርዋም አበሰች። አንተ አልሳምኸኝም፤ እርስዋ ግን ከገባሁ ጀምራ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም። አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች።
ያጋሩ
ሉቃስ 7 ያንብቡ