“ወደ እኔ የሚመጣ ሁሉ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሕይወት እንኳ ከእኔ አብልጦ የሚወድ ከሆነ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም። የራሱን መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ፥ የእኔ ደቀ መዝሙር ሊሆን አይችልም። “ከእናንተ መካከል አንዱ ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለሥራው ማስፈጸሚያ ምን ያኽል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስቀድሞ የማያስብ ማነው? መሠረቱን ጥሎ የሕንጻውን ሥራ መፈጸም ያልቻለ እንደ ሆነ ግን በጅምር የቀረውን ቤት የሚያዩት ሁሉ ይዘባበቱበታል፤ ‘እነሆ፥ ይህ ሰው ቤት መሥራት ጀምሮ መጨረስ አልቻለም’ እያሉ ያፌዙበታል። “ዐሥር ሺህ ወታደር ያለውን አንድ ንጉሥ ኻያ ሺህ ወታደር አስከትቶ ከሚመጣበት ሌላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ቢፈልግ መጀመሪያ ጠላቱን ለመቋቋም የሚችል መሆኑን ለማወቅ ተቀምጦ ይማከራል። የማይችል ከሆነ ግን ሊወጋው የሚመጣው ንጉሥ ገና በሩቅ ሳለ ይህ ንጉሥ የሰላም መልእክተኞችን ወደ እርሱ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል። እንዲሁም ከእናንተ መካከል ያለውን ሁሉ ለእኔ ሲል ያልተወ ማንም ሰው የእኔ ደቀ መዝሙር መሆን አይችልም።”
የሉቃስ ወንጌል 14 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የሉቃስ ወንጌል 14:26-33
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች