እግዚአብሔር ለአሚታይ ልጅ ለዮናስ የገለጠለት የትንቢት ቃል ይህ ነው፦ “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የሕዝብዋን ክፋት ተመልክቼአለሁ። ድምፅህንም ከፍ አድርገህ እርስዋን በመገሠጽ ተናገር።” ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር። እግዚአብሔር ግን በባሕሩ ላይ ከባድ ነፋስን አስነሣ፤ በባሕሩም ላይ የተቀሰቀሰው ማዕበል ብርቱ ከመሆኑ የተነሣ መርከቢቱ ልትሰበር ተቃረበች፤ መርከበኞቹም እጅግ ስለ ፈሩ እያንዳንዱ ወደ አምላኩ ጮኸ፤ የመርከቢቱን ክብደት ለመቀነስ አስበው በውስጥዋ የነበረውን ዕቃ እያወጡ ወደ ባሕር ጣሉ፤ ዮናስ ግን በመርከቢቱ ታችኛ ክፍል ወርዶ በመተኛቱ በከባድ እንቅልፍ ላይ ነበር። የመርከብ አዛዡም ወደ እርሱ ቀርቦ “እንዴት ትተኛለህ? ኧረ እባክህ ተነሥና ወደ አምላክህ ጸልይ፤ ምናልባት ራርቶልን ሕይወታችንን ያድን ይሆናል” አለው።
ትንቢተ ዮናስ 1 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ዮናስ 1:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos