የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ወንጌል 4:27-30

የዮሐንስ ወንጌል 4:27-30 አማ05

በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ከሄዱበት ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ “ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?” ብሎ የጠየቀው ማንም አልነበረም። ከዚህ በኋላ ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ሄደችና ለሰዎቹ እንዲህ አለች፦ “የሠራሁትን ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑ እዩ! ምናልባት እርሱ መሲሕ ይሆንን?” ሰዎቹም ከከተማ ወጥተው ወደ ኢየሱስ ሄዱ።