እግዚአብሔር የይሁዳ ሕዝብ ወደሚሰግዱበት ወደ ቤተ መቅደሱ የቅጽር በር ላከኝ፤ በዚያ ቆሜ እንድነግራቸው ያዘዘኝ ቃል ይህ ነው፦ “የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እኔም በዚህች ምድር እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነው! እኛም በሰላም እንኖራለን!’ በምትሉት ከንቱ ቃላችሁ አትታመኑ። “ይልቅስ የአኗኗራችሁንና የተግባራችሁን ሁኔታ ለውጡ፤ እርስ በርሳችሁ ቅንነት በሞላበት ፍቅር ተሳስራችሁ ኑሩ፤ መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ። በዚህ ዐይነት ለውጥ የምታሳዩ ከሆነ ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለዘለዓለም ርስት አድርጌ በሰጠኋቸው በዚህች ምድር እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ። “ተመልከቱ! እናንተ እኮ በሚያታልሉ ከንቱ ቃላት ትተማመናላችሁ፤ ከዚህም የተነሣ ትሰርቃላችሁ፤ ትገድላላችሁ፤ ታመነዝራላችሁ፤ ምላችሁም በሐሰት ትመሰክራላችሁ፤ ለባዓል መሥዋዕት ታቀርባላችሁ፤ ከዚህ በፊት የማታውቁአቸውን አማልክት ታመልካላችሁ። እኔ የምጠላውን ይህን ሁሉ ነገር ከፈጸማችሁ በኋላ ወደ ቤተ መቅደሴ መጥታችሁ በፊቴ በመቆም ‘እኛ ከጥፋት ድነናል!’ ትላላችሁ። ቤተ መቅደሴ የሌቦች መደበቂያ ዋሻ መሰላችሁን? የምታደርጉትን ሁሉ እነሆ እኔ ራሴ አይቼአለሁ፤
ትንቢተ ኤርምያስ 7 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኤርምያስ 7:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች