መጽሐፈ መሳፍንት 1:27-36

መጽሐፈ መሳፍንት 1:27-36 አማ05

የምናሴ ነገድ ቤትሻን፥ በታዕናክ በዶርን የዪብልዓምንና በመጊዶና በአካባቢያቸው የሚኖሩትን ሰዎች አላስወጡም ነበር፤ ከነዓናውያንም በዚያው መኖርን ቀጠሉ፤ እስራኤላውያን ብርታት ባገኙ ጊዜ ከነዓናውያን ለእነርሱ የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር፤ ሆኖም ሁሉንም አላስወጡም ነበር። የኤፍሬም ነገድም በጌዜር ይኖሩ የነበሩትን ከነዓናውያንን አላባረሩም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ። የዛብሎን ነገድ በቂትሮንና በናህላል ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላስወጡም ነበር፤ ስለዚህ ከነዓናውያን እዚያው ከእነርሱ ጋር ኗሪዎች ሆኑ፤ ሆኖም ለዛብሎናውያን የጒልበት ሥራ ለመሥራት ይገደዱ ነበር። የአሴር ነገድ በዓኮ፥ በሲዶና፥ በአሕላብ፥ በአክዚብ፥ በሔልባ፥ በአፌቅና በረሖብ ይኖሩ የነበሩትን ኗሪዎች አላባረሩም ነበር። ከነዓናውያንንም ሳያስወጡ በመቅረታቸው የአሴር ሕዝብ በዚያው ከእነርሱ ጋር አብረው ይኖሩ ነበር። የንፍታሌም ነገድ በቤትሼሜሽና በቤትዓናት ይኖሩ የነበሩትን ሰዎች አላስወጡም፤ ስለዚህም የንፍታሌም ሕዝብ ከከነዓናውያን ጋር እዚያው አብረው መኖርን ቀጠሉ፤ ሆኖም የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ከነዓናውያንን ያስገድዱአቸው ነበር። አሞራውያን የዳንን ነገድ ሕዝብ ወደ ኮረብታማው አገር አባረሩአቸው፤ ወደ ሜዳማውም ምድር እንዲወርዱ አልፈቀዱላቸውም፤ አሞራውያን በሔሬስ ተራራና በአያሎን፥ በሻዓልቢም መኖርን ቀጠሉ፤ ነገር ግን የዮሴፍ ልጆች (የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች) የእነርሱ ተገዢዎች አድርገው የጒልበት ሥራ እንዲሠሩላቸው ያስገድዱአቸው ነበር። የአሞራውያን ድንበር ከዐቅራቢም አቀበት ከሴላዕ ጀምሮ ወደ ላይ ይወጣ ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}