ወንድሞቼ ሆይ! እኛ አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁና ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ። እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው። ፈረስ እንዲታዘዝልን በአፉ ውስጥ ልጓም እናገባለን፤ ፈረሱንም ወደምንፈልገው ቦታ እንመራዋለን። መርከብ ምንም ትልቅ ቢሆንና በኀይለኛ ነፋስ የሚገፋ ቢሆንም፥ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መቅዘፊያ ወደ ፈለገው ቦታ ይነዳዋል። እንዲሁም ምላስ ትንሽ የአካል ክፍል ስትሆን በታላላቅ ነገሮች ትመካለች፤ ትልቅ ጫካ የሚቃጠለው በትንሽ እሳት ነው። ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች። የምድር አውሬዎችና ወፎች፥ በመሬት የሚሳቡና በባሕር የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሁሉ በሰው ሊገሩ ይችላሉ፤ ደግሞም ተገርተዋል። ነገር ግን ምላስን ሊገራ የሚችል ማንም የለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላባትና ዕረፍት የሌላት ክፉ ነገር ናት። በእርስዋ አባታችንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፤ እንዲሁም በእርስዋ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን። ከአንድ አፍ ምስጋናና ርግማን ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም። ከአንድ ምንጭ ለመጠጥ የሚሆን ጣፋጭ ውሃና መራራ ውሃ ሊፈልቅ ይችላልን? ወንድሞቼ ሆይ፥ የበለስ ዛፍ የወይራን ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? ወይስ የወይን ተክል የበለስ ፍሬ ሊያፈራ ይችላልን? እንዲሁም ከመራራ ውሃ ጣፋጭ ውሃ ሊገኝ ይችላልን?
የያዕቆብ መልእክት 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የያዕቆብ መልእክት 3:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች