የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ኢሳይያስ 45:1-7

ትንቢተ ኢሳይያስ 45:1-7 አማ05

ሕዝቦች በሥልጣኑ ሥር እንዲገዙ ለማድረግ፥ ነገሥታትን ከሥልጣን እንዲያወርድ፥ የከተሞችን ቅጽር በሮች ይከፍትለት ዘንድ ቀኝ እጁን ለያዘውና ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥ ቂሮስን እግዚአብሔር እንዲህ ይለዋል፦ “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራራዎችን ዝቅ አድርጌ እደለድላለሁ፤ በነሐስ የተሠሩ በሮችንና የብረት መወርወሪያዎችን እሰብራለሁ። በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ። የመረጥኳቸውን የያዕቆብን ልጆች እስራኤላውያንን እንድትረዳ፥ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ የማዕርግ ስምም ሰጥቼሃለሁ። “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አንተ እኔን ባታውቀኝም እንኳ ብርታትን እሰጥሃለሁ። ይህንንም የማደርገው መላው ዓለም እኔ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቅ ዘንድ ነው። እኔ ጨለማንና ብርሃንን እፈጥራለሁ፤ ደኅንነትንና ወዮታን አመጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አደርጋለሁ።