ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18-21

ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18-21 አማ05

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ያለፉትን ድርጊቶች አታስታውሱ፤ ከዚህ በፊት የሆነውንም ነገር አታሰላስሉ። ይልቅስ የማደርገውን አዲስ ነገር ተመልከቱ፤ እርሱም በመፈጸም ላይ ስለ ሆነ ልታዩት ትችላላችሁ፤ በበረሓ መንገድን አወጣለሁ፤ በምድረ በዳም ወንዞችን አፈልቃለሁ። ለተመረጡት ሕዝቤ ውሃን ለመስጠት ወንዞች በበረሓ ጅረቶች በምድረ በዳ እንዲፈስሱ ባደረግሁ ጊዜ የምድር አራዊት እንኳ ሳይቀሩ ያከብሩኛል፤ ቀበሮዎችና ሰጎኖችም ያመሰግኑኛል። እነርሱም ለራሴ የሠራኋቸው ሕዝቦች ስለ ሆኑ እኔን ያመሰግናሉ።”