የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ሆሴዕ 6

6
እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ ለንስሓ መጥራቱ
1ሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “ኑ! ወደ እግዚአብሔር እንመለስ! እርሱ እንደ ሰበረን ይፈውሰናል፤ እርሱ እንዳቈሰለን ቊስላችንን ይጠግናል። 2በፊቱ በሕይወት እንኖር ዘንድ፥ ከሁለት ቀን በኋላ ያድሰናል፤ በሦስተኛው ቀን ያስነሣናል፤ 3ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
4እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! እናንተን ምን ላድርጋችሁ? እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር እንደ ማለዳ ጉምና እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ይጠፋል። 5በነቢያቴ አማካይነት እንደማጠፋቸው በቃሌም አማካይነት እንደምገድላቸው አስጠነቀቅኋቸው፤ ስለዚህ ፍርዴ እንደ ንጋት ብርሃን ያንጸባርቃል። 6እኔ ከመሥዋዕት ይልቅ የማይለዋወጥ ፍቅርን እወዳለሁ፤ ከሚቃጠል መሥዋዕት ይልቅ እኔን እግዚአብሔርን ማወቃችሁን እመርጣለሁ። #ማቴ. 9፥13፤ 12፥7።
7“እነርሱ ወደ አገሪቱ በገቡ ጊዜ ‘አዳም’ በምትባል ቦታ ከእኔ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፈረሱ፤ ለእኔ የማይታመኑ መሆናቸውንም ገለጡ። 8ገለዓድ ክፉ ሰዎችና በደም የተበከሉ ነፍሰ ገዳዮች የሞሉባት ከተማ ሆናለች! 9ወንበዴዎች ሰውን ለመግደል እንደሚያደቡ የካህናቱም ቡድን እንዲሁ ያደርጋል፤ ወደ ሴኬም በሚወስደው መንገድ እንኳ እያደቡ ሰውን ይገድላሉ፤ አሳፋሪም የሆነ ወንጀል ይፈጽማሉ። 10እጅግ የሚያሠቅቅ ነገር በእስራኤል ሕዝብ ዘንድ አይቼአለሁ፤ ይኸውም ሕዝቡ ጣዖትን በማምለክ ዝሙት ረክሶአል።
11“እናንተ የይሁዳ ሕዝብ ሆይ!
በእናንተም ላይ የፍርድ ቀን ወስኜአለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ