የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 39:7-20

ኦሪት ዘፍጥረት 39:7-20 አማ05

ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስለ አፈቀረችው፥ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው። እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ ስለዚህም እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሁሉንም ነገር በእኔ ኀላፊነት ሥር ስላደረገ፥ በቤቱ ውስጥ ስላለው ንብረት ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፤ ያለውን ንብረት ሁሉ እንዳስተዳድርለት በዐደራ ለእኔ ሰጥቶኛል። ጌታዬ በዚህ ቤት ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ከእኔ የበለጠ ኀላፊነት የለውም፤ ከአንቺ በቀር በእኔ ቊጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለ ሆንሽ ነው፤ ታዲያ ይህን አስከፊ ኃጢአት በመፈጸም እግዚአብሔርን እንዴት አሳዝናለሁ?” እርስዋም ይህንኑ ጉዳይ በየቀኑ ትነግረው ነበር፤ ዮሴፍ ግን አብሮአት መተኛት ወይም በአጠገቧ ለመገኘት አልፈለገም። ከዕለታት አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም። በዚያን ጊዜ የጌታው ሚስት ልብሱን ይዛ “ከእኔ ጋር ተኛ” አለችው፤ እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ። እርስዋም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፥ አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፤ “እነሆ፥ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደን ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽኩ። ርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን አጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።” የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቈየችው። በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፥ “አንተ ወደዚህ ያመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር። ነገር ግን ርዳታ ለማግኘት ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽኩ ጊዜ ልብሱን አጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።” ሚስቱ “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቈጣ። ስለዚህ ዮሴፍን ወስዶ የንጉሡ እስረኞች ወዳሉበት እስር ቤት አስገባው። ነገር ግን ዮሴፍ በእስር ቤት በነበረበት ጊዜ፥

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}