የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 33:4-11

ኦሪት ዘፍጥረት 33:4-11 አማ05

ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጠ፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ዕቅፍ አድርጎ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ። ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ። ከዚህ በኋላ ሴቶች አገልጋዮቹ ከልጆቻቸው ጋር መጥተው እጅ ነሡ። ቀጥሎም ልያና ልጆችዋ ቀርበው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል ቀርበው እጅ ነሡ። ዔሳውም “እፊት እፊትስ እየተነዳ ሲሄድ ያየሁት የእንስሶች መንጋ ምንድን ነው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እርሱ በአንተ ፊት ሞገስ እንዳገኝ የላክሁልህ ነው” አለ። ዔሳውም “ወንድሜ ሆይ፥ እኔ በቂ ሀብት አለኝ፤ የአንተ ለራስህ ይሁን” አለው። ያዕቆብ ግን “እንዲህስ አይሁን፤ በእርግጥ የምትወደኝ ከሆነ እባክህ ስጦታዬን ተቀበል፤ ፍቅር ስላሳየኸኝ፥ የአንተን ፊት ማየት የእግዚአብሔርን ፊት እንደማየት ያኽል እቈጥረዋለሁ። ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}