ይስሐቅ አብርሃምን “አባባ!” አለው፤ አብርሃምም “እነሆ፥ አለሁ ልጄ!” አለው። ይስሐቅም “እነሆ፥ እሳትና እንጨት ይዘናል፤ ታዲያ ለመሥዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ?” በማለት አብርሃምን ጠየቀው። አብርሃምም “ልጄ ሆይ፥ ለመሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ለራሱ ያዘጋጃል” አለው፤ ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው።
ኦሪት ዘፍጥረት 22 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ኦሪት ዘፍጥረት 22:7-9
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች