ዘፍጥረት 22:7-9

ዘፍጥረት 22:7-9 NASV

ይሥሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይሥሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት በግ የት አለ?” ብሎ ጠየቀ። አብርሃምም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለሚቃጠለው መሥዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር ያዘጋጃል” አለው። ሁለቱም ዐብረው ጕዟቸውን ቀጠሉ። እግዚአብሔር ወደ አመለከተው ቦታ እንደ ደረሱ፣ አብርሃም መሠዊያ ሠራ፤ በላዩም ላይ ዕንጨት ረበረበ፤ ልጁን ይሥሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ዕንጨት ላይ አጋደመው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}