ኦሪት ዘፍጥረት 13:14-17

ኦሪት ዘፍጥረት 13:14-17 አማ05

ሎጥ ከሄደ በኋላ እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ስፍራ ሆነህ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ፥ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት፤ ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ እሰጣችኋለሁ፤ ለዘለዓለምም የእናንተ ይሆናል፤ ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ የምድር አሸዋ ሊቈጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር እንዲሁ ሊቈጠር የማይቻል ይሆናል። ተነሥተህ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ሂድ፤ ሁሉንም ለአንተ እሰጥሃለሁ።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}