ኦሪት ዘፍጥረት 12:1-5

ኦሪት ዘፍጥረት 12:1-5 አማ05

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤ ዘርህን አበዛዋለሁ፤ ታላቅ ሕዝብም ይሆናል፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህንም ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት ትሆናለህ። የሚመርቁህን እመርቃለሁ፤ የሚረግሙህንም እረግማቸዋለሁ፤ በአንተም አማካይነት ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።” አብራም እግዚአብሔር እንደ ነገረው ከካራን ወጥቶ ሄደ፤ በዚያን ጊዜ ዕድሜው ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}