ዘፍጥረት 12:1-5

ዘፍጥረት 12:1-5 NASV

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ከአገርህ ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ። የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህን ረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም፣ በአንተ ይባረካሉ።” ስለዚህ አብራም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም ዐብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ሲወጣ ዕድሜው 75 ዓመት ነበረ። አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ሳሉ ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዘው በመጓዝ ከነዓን ምድር ገቡ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}