“እንግዲህ እነሆ፥ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምልህን ሁሉ ንገራቸው፤ ከእንግዲህ ወዲህ የማደርግላችሁ ነገር በሄዳችሁበት ስፍራ ሁሉ ስላሰደባችሁት ስለ ቅዱስ ስሜ እንጂ ስለ እናንተ ስለ እስራኤላውያን ብዬ አይደለም። በሕዝቦች መካከል ተሰድቦ የነበረውን፥ ማለት እናንተ አሰደባችሁት የነበረውን የታላቁን ስሜን ቅድስና አሳያለሁ፤ ከዚያ በኋላ በእናንተ አማካይነት በእነርሱ ፊት ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ ሕዝቦች እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ። ከመንግሥቶች ከአገሮች ሁሉ አውጥቼ በመሰብሰብ ወደ ገዛ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ። በእናንተ ላይ ንጹሕ ውሃ በመርጨት ከጣዖት አምልኮአችሁና ከርኲሰታችሁ ሁሉ እንድትነጹ አደርጋለሁ። አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስንም በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ ከሰውነታችሁ እንደ ድንጋይ የጠጠረ ልብን አውጥቼ እንደ ሥጋ የለሰለሰ ልብን እሰጣችኋለሁ። መንፈሴን አሳድርባችኋለሁ፤ የሰጠኋችሁንም ሕግና ሥርዓት ሁሉ በጥንቃቄ መፈጸም እንድትችሉ አደርጋችኋለሁ። ከዚያም በኋላ ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ እናንተ ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ። ከርኲሰታችሁ ነገር ሁሉ አድናችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ራብ እንዳይደርስባችሁ እህል እንዲበዛላችሁ አዛለሁ። የዛፋችሁና የእርሻችሁ ፍሬ ሁሉ እንዲበዛ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ እናንተን በአሕዛብ መካከል የሚያዋርድ ራብ አይደርስባችሁም። መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ። እኔ የማደርገውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ብዬ የማላደርግ መሆኔ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ስለዚህ እስራኤል ሆይ! በአካሄዳችሁ ኀፍረትና ውርደት ይሰማችሁ።” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።
ትንቢተ ሕዝቅኤል 36 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ሕዝቅኤል 36:22-32
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos