ኦሪት ዘጸአት 21:20-24

ኦሪት ዘጸአት 21:20-24 አማ05

“አንድ ሰው ወንድም ሆነ ሴት ባሪያውን በበትር ቢመታና ወዲያው ቢሞትበት መቀጣት ይገባዋል፤ ነገር ግን ባሪያው በአንድ ቀን ወይም በሁለት ቀን ውስጥ ባይሞት አሳዳሪ ጌታው አይቀጣም፤ ባሪያውን ማጣቱ ራሱ ቅጣት ነው። “ሁለት ሰዎች ሲጣሉ አንዲት ነፍሰ ጡር መተው ቢያስወርዳትና ሌላ ምንም ጒዳት ሳይደርስባት ቢቀር፥ ያ ጒዳት ያደረሰባት ሰው የሴቲቱ ባል የሚጠይቀውን ያኽል ካሣ ይክፈል፤ ይህም የሚከፍለው ካሣ መጠን በዳኞች የጸደቀ ይሁን። ነገር ግን ሴትዮዋ ራስዋ ብርቱ ጒዳት የደረሰባት ከሆነች ቅጣቱ ‘በሕይወት ምትክ ሕይወት፥ በዐይን ምትክ ዐይን፥ በጥርስ ምትክ ጥርስ፥ በእጅ ምትክ እጅ፥ በእግር ምትክ እግር፥

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}