የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘጸአት 17:1-7

ኦሪት ዘጸአት 17:1-7 አማ05

መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም። ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። ሕዝቡ ግን እጅግ ተጠምተው ስለ ነበር “ከግብጽ ምድር ያወጣኸን ለምንድን ነው? እኛንና ልጆቻችንን እንስሶቻችንንም ጭምር በውሃ ጥም ለመፍጀት ነውን?” እያሉ በሙሴ ላይ ማጒረምረማቸውን ቀጠሉ። ሙሴም “ከቶ ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻላል? እነሆ፥ በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” እያለ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች፥ ጥቂቶቹን ውሰድ፤ ከሕዝቡም ቀድመህ ወደ ፊት ሂድ፤ የዐባይን ወንዝ የመታህበትንም በትር በእጅህ ያዝ፤ እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ። እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}