የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፀአት 17:1-7

ዘፀአት 17:1-7 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም። ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። ሕዝቡ ግን እጅግ ተጠምተው ስለ ነበር “ከግብጽ ምድር ያወጣኸን ለምንድን ነው? እኛንና ልጆቻችንን እንስሶቻችንንም ጭምር በውሃ ጥም ለመፍጀት ነውን?” እያሉ በሙሴ ላይ ማጒረምረማቸውን ቀጠሉ። ሙሴም “ከቶ ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻላል? እነሆ፥ በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” እያለ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች፥ ጥቂቶቹን ውሰድ፤ ከሕዝቡም ቀድመህ ወደ ፊት ሂድ፤ የዐባይን ወንዝ የመታህበትንም በትር በእጅህ ያዝ፤ እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ። እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ።

ዘፀአት 17:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም። ሕዝ​ቡም ሙሴን ተጣ​ሉት፥ “የም​ን​ጠ​ጣ​ውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ለምን ትፈ​ታ​ተ​ና​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ። ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕ​ዝቡ ፊት እለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ወን​ዙ​ንም የመ​ታ​ህ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ይዘ​ሃት ሂድ። እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮ​ሬብ በዓ​ለት ላይ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፤ ዓለ​ቱ​ንም ትመ​ታ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ይጠጣ ዘንድ ከእ​ርሱ ውኃ ይወ​ጣል” አለው። ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዲሁ አደ​ረገ። ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው።

ዘፀአት 17:1-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም። ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ። ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብጽ ለምን አወጣኸን?” አሉት። ከዚያም ሙሴ፤ “በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ መለሰለት፤ “ከሕዝቡ ፊት ሂድ፤ ከእስራኤል አለቆች አንዳንዶቹን እንዲሁም አባይን የመታህባትን በትር ያዝና ሂድ። ኮሬብ አጠገብ ባለው ዐለት በዚያ እኔ በአንተ ፊት እቆማለሁ። ዐለቱን ምታው፤ ከርሱም ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ ይወጣል።” ስለዚህ ሙሴ በእስራኤል አለቆች ፊት ይህንኑ አደረገ። ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።

ዘፀአት 17:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው። ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፦ እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኽን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጎራጎሩ። ሙሴም፦ ሊወግሩኝ ቀርበዋልና በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአሔርም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ። እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ። ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው።

ዘፀአት 17:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ጌታ እንዳዘዘ ሊጓዙ ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፥ በረፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉት። ሙሴም፦ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? ጌታንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ። ሙሴም፦ “ይህን ሕዝብ ምን ላድርገው? በድንጋይ ሊወግሩኝ ቀርበዋል” ብሎ ወደ ጌታ ጮኸ። ጌታም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ የዓባይን ወንዝ የመታህበትን በትር በእጅህ ይዘህ ሂድ። እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ። እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው።