የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘጸአት 15:12-18

ኦሪት ዘጸአት 15:12-18 አማ05

ቀኝ እጅህን በዘረጋህ ጊዜ ጠላቶቻችንን ምድር ዋጠቻቸው፤ በማይለወጥ ፍቅርህ ያዳንካቸውን ሕዝብ መራህ፤ በብርታትህም ወደ ተቀደሰችው ምድር እንዲገቡ አደረግህ፤ አሕዛብ ሁሉ ይህን ሰምተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ ፍልስጥኤማውያንም ተሸበሩ፤ የኤዶም መሪዎች ተስፋ ቈረጡ፤ የሞአብም ኀያላን ተንቀጠቀጡ፤ የከነዓንም ሕዝብ ወኔ ከዳቸው። አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ። አምላክ ሆይ፥ ለማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ እጆችህ ባዘጋጁት መቅደስ፥ ወገኖችህን አንተ ታስገባቸዋለህ፤ በርስትህ ተራራም ትተክላቸዋለህ። እግዚአብሔር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}