“ቀኝ እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው። በማይለወጠው ፍቅርህ፣ የተቤዥሃቸው ሕዝብህን ትመራለህ፤ እነርሱን በብርታትህ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ ትመራቸዋለህ። አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል። የኤዶምም አለቆች ይርዳሉ፤ የሞአብ አለቆች በእንቅጥቃጤ ይያዛሉ፤ የከነዓን ሕዝብ ይቀልጣሉ። አቤቱ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠኻቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ። እግዚአብሔር (ያህዌ) ሆይ፤ ማደሪያህ እንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ ጌታ (አዶናይ) ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም። “እግዚአብሔር (ያህዌ)፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣል።”
ዘፀአት 15 ያንብቡ
ያዳምጡ ዘፀአት 15
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ዘፀአት 15:12-18
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos