መጽሐፈ አስቴር 6:12-14

መጽሐፈ አስቴር 6:12-14 አማ05

ከዚህ በኋላ መርዶክዮስ ወደ ቤተ መንግሥቱ መግቢያ ተመልሶ ሲሄድ፥ ሃማን ከኀፍረቱ ብዛት የተነሣ ራሱን በመከናነብ ወደ መኖሪያ ቤቱ ፈጥኖ ሄደ። ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት። እነርሱም ገና ይህን በመነጋገር ላይ ሳሉ የቤተ መንግሥቱ ጃንደረቦች ሃማንን ወደ አስቴር ግብዣ በአስቸኳይ ይዘውት ሄዱ።