አስቴር 6:12-14
አስቴር 6:12-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም በኋላ መርዶክዮስ ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ፤ ሐማ ግን ዐዝኖና ራሱን ተከናንቦ በጥድፊያ ወደ ቤቱ ሄደ። ሐማም የደረሰበትን ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው። አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት። ከርሱ ጋራ በመነጋገር ላይ ሳሉ፣ የንጉሡ ጃንደረቦች ደርሰው ሐማን አስቴር ወዳዘጋጀችው ግብዣ አጣደፉት።
አስቴር 6:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
መርዶክዮስም ወደ ንጉሡ በር ተመለሰ። ሐማ ግን አዝኖና ራሱን ተከናንቦ ቸኵሎ ወደ ቤቱ ሄደ። ሐማም ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ያገኘውን ሁሉ አጫወታቸው። ጥበበኞቹና ሚስቱ ዞሳራም፦ በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ከአይሁድ ወገን የሆነ እንደ ሆነ በፊቱ ፈጽሞ ትወድቃለህ እንጂ አታሸንፈውም አሉት። እነርሱም ሲናገሩት ሳሉ እነሆ የንጉሡ ጃንደረቦች መጡ፥ አስቴርም ወዳዘጋጀችው ግብዣ ይመጣ ዘንድ ሐማን አስቸኰሉት።

አስቴር 6:12-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህ በኋላ መርዶክዮስ ወደ ቤተ መንግሥቱ መግቢያ ተመልሶ ሲሄድ፥ ሃማን ከኀፍረቱ ብዛት የተነሣ ራሱን በመከናነብ ወደ መኖሪያ ቤቱ ፈጥኖ ሄደ። ለሚስቱና ለወዳጆቹም የደረሰበትን አሳፋሪ ነገር በሙሉ ነገራቸው፤ ሚስቱና እነዚያ አስተዋዮች የሆኑ ወዳጆቹም “እነሆ በገዛ እጅህ ሥልጣንህን ለመርዶክዮስ ልታስረክብ ተቃርበሃል፤ እርሱ አይሁዳዊ ስለ ሆነ ልትቋቋመው አትችልም፤ በእርግጥም እርሱ ያሸንፍሃል!” አሉት። እነርሱም ገና ይህን በመነጋገር ላይ ሳሉ የቤተ መንግሥቱ ጃንደረቦች ሃማንን ወደ አስቴር ግብዣ በአስቸኳይ ይዘውት ሄዱ።