ጾም በጀመረች በሦስተኛውም ቀን አስቴር ልብሰ መንግሥትዋን ለብሳ በዙፋኑ ክፍል ፊት ለፊት ወደሚገኘው ወደ ውስጠኛው የቤተ መንግሥት አደባባይ ገብታ ቆመች፤ ንጉሡም በዚያው ክፍል ውስጥ ከመግቢያው በር ፊት ለፊት በተዘረጋ ዙፋን ላይ ተቀምጦ ነበር። ንጉሡ፥ ንግሥት አስቴር በስተ ውጪ በኩል መቆምዋን በተመለከተ ጊዜ በፊቱ ሞገስን አግኝታ ስለ ነበር የወርቅ በትሩን ዘረጋላት፤ እርስዋም ቀረብ ብላ የወርቁን በትር ጫፍ ነካች። ንጉሡም “አስቴር ሆይ፥ ስለምን መጣሽ? ምን እንደምትፈልጊ ንገሪኝ፤ የንጉሠ ነገሥት መንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ቢሆን እሰጥሻለሁ” አላት። አስቴርም “ንጉሥ ሆይ! መልካም ፈቃድህ ቢሆን ለዛሬ ማታ ባዘጋጀሁት ግብዣ ላይ አንተና ሃማን ብትገኙልኝ እወዳለሁ” አለችው። ከዚህም በኋላ ንጉሡ ሃማንን በፍጥነት አስጠርቶ በአስቴር ግብዣ ላይ መገኘት እንዳለባቸው ነገረው፤ ስለዚህም ንጉሡና ሃማን ወደ አስቴር ግብዣ አመሩ። የወይን ጠጅ በመጠጣት ላይ ሳሉም ንጉሡ አስቴርን “ማናቸውንም የምትፈልጊውን ነገር ጠይቂኝ፤ ይፈጸምልሻል፤ የመንግሥቴን እኩሌታ እንኳ ብትጠይቂ ልሰጥሽ ዝግጁ ነኝ!” አላት። አስቴርም እንዲህ ስትል መለሰችለት፦ “በግርማዊነትዎ ፊት ሞገስ አግኝቼ ግርማዊነትዎ የጠየቅሁትን ነገር ሊፈጽምልኝ ፈቃደኛ ከሆነ ነገ በማዘጋጀው ግብዣ ላይ እርስዎና ሃማን በድጋሚ እንድትገኙልኝ በአክብሮት እለምናለሁ፤ በዚያም ሰዓት የምፈልገውን ነገር እገልጥልዎታለሁ።”
መጽሐፈ አስቴር 5 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ አስቴር 5:1-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos