ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:30-33

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:30-33 አማ05

እኛም የክርስቶስ አካል ክፍሎች ነን፤ “በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎአል። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፤ ይህንንም የምለው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ ነው። ነገር ግን ይህ ነገር እናንተንም ይመለከታል፤ ስለዚህ ባል ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ ይውደድ፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።